የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጸዋትወ ዜማ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፥ አሜን።
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጸዋትወ ዜማ
ዜማ ማለት በልዩ ኅብር የተቀነባበረ ድምፅ ማለትም በከፍተኛውና በዝቅተኛው የድምፅ መያያዝ መካከል ያለው ቃና ነው። በሌላ በኩል
ደግሞ ጣዕም፣ ለዛና ስልት ኖሮት በድምፅ ተቀነባብሮና ተስማምቶ ልዩ ስሜትና ተመስጦ ሊሰጥ በሚችል መልኩ የሚያሰሙት ቅንብር
(ድምፅ) ነው።
የዜማ አጀማመር፦ ዜማ የተጀመረው በጥንተ ፍጥረት ሲሆን መላእክት እንደተፈጠሩ ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል (ኢዮ qr፥፮)
ዜማ በመጽሐፍ ቅዱስ፦ ዜማ ተወዳጅ የሆነ የመንፈስ ምግብ ነውና ሰዎች ከጥንተ ፍጥረት ጀምሮ ሲጠቀሙበት ኖረዋል። (ዘፍጥ ፬፥
z{) በዘመነ ሐዲስም ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሐዋርያቱ ጋር ለፋሲካ እራት ከተቀመጡ በኋላ መዝሙር
መዘመራቸውን ተጽፎ እናገኛለን። (ማቴ zã፥፴)
ዜማ በቅዱስ ያሬድ፦ ኢትዮጵያ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ የክርስትና ሃይማኖት በብሔራዊ ደረጃ ስትቀበል
ለምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ማስፈጸሚያ የሚሆን ክርስቲያናዊ ዜማ ነበራት። ይህ ዜማ በሌሎች አብያተ ክርስቲያናት እንደሚታየው
ለአገልግሎት ማስፈጸሚያ ያህል በመጠኑ ያገለግል የነበረ ዜማ እንጂ እንደ አሁኑ ጥልቀት ያለው የተደራጀና የተቀነባበረ ዜማ
አልነበረም።
ዜማ በቅዱስ ያሬድ፦ ቅዱስ ያሬድ በõúù ዓ.ም. የተወለደ ኢትዮጵያ ሊቅ ነው። ቅዱስ ያሬድ በመንፈስ ቅዱስ የተቃኘ የመንፈሳዊ ዜማ
ደራሲ፣ የቅኔ ተመራማሪ እንዲሁም የተወደደ ድምፀ መልካም ማኅሌታዊ ነው።
የቅዱስ ያሬድ ድርሰቶች፦
ሀ) ዝማሬ – ዝማሬ “ዘመረ፥ አመሰገነ” ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ነው። ይህ ድርሰት ለአገልግሎት የሚውለው በቅዳሴ ጊዜ ልክ እንደ
መልክአ ቁርባን ሆኖ ከክብር ይእቲ በኋላ ነው።
ለ) መዋሥዕት – “አውሥአ” ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን “ምልልስ” ማለት ነው። ምክንያቱም አባባሉ በግራና በቀኝ
እየተመላለሰና እየተቀባበለ ስለሚባል ነው። በሥራ ላይ የሚውለው ለዕለተ ፍትሐት እንዲሁም ለሙት ዓመት ነው። በተጨማሪም
በጥምቀት ዋዜማ፣ በበዓለ ሆሳዕና፣ በቀዳም ሥዑር፣ በጌታችን እንዲሁም በእመቤታችን በፃድቃን በሰማዕታት በዓላት ሁሉ ላይ
ለአገልግሎት ሊውል ይችላል።
ሐ) ምዕራፍ – “ማረፊያ፣ ማሳረፊያ፣ መቀመጫ” ማለት ነው። አገልግሎቱ የዘወትር እና የጾም ምዕራፍ ተብሎ ለሁለት ይከፈላል።
የዘወትር የሚባለው በዓመቱ ውስጥ ባሉት ሳምንታትና በዓላት ወቅቱን እየጠበቀ በአገልግሎት ላይ የሚውል ሲሆን የጾም ምዕራፍ
የሚባለው ደግሞ በጾመ ሁዳዴ እና በአንዳንድ የምህላ ቀኖች የሚያገለግል ነው።
መ) ድጓ – ጽሕፈቱ የረቀቀ፣ የደቀቀ የዜማ ስልት ማለት ነው። ላላ ተብሎ ሲነበብ ደግሞ “ድጓ ለቤተ ክርስቲያን” ሲል የቤተ ክርስቲያን
ትጥቋ፣ መቀነቷ እንደማለት ነው። ድጓውም እንደ ወንጌል በአራት ዐቢይ ክፍላት ይከፈላል፦ ድጓ ዘዮሐንስ፣ ዘአስተምህሮ፣ ዘጾም፣
ዘፋሲካ ይባላሉ። የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ድጓውን ተከትሎ ስለሚሄድ ይትበሃሉን ማወቅና መከተል ያስፈልጋል።
ሠ) ጾመ ድጓ – የሚዘመረው በዐቢይ ጾም ከዘወረደ ጀምሮ እስከ በዓለ ትንሣኤ ድረስ ነው። የዜማው ስልትና አቀነባበር በትምህርት
ሲከተሉት የምሥጢሩ ጥልቀት፣ የትርጓሜው ስፋት የሚዘምሩትን ሊቃውንትና መምህራንን ህሊና እንዲሁም የሰማዕያን
(የአድማጮችን) ምእመናን ሁሉ ልቡና በመንፈሳዊ ስሜት የሚመስጥ ነው።
እኒህ ከላይ የተጠቀሱት ድርሰቶች ውስጥ ያሉ ዜማዎች የሚዜሙት በምልክት ነው። አሥር የመሆናቸውም ምሥጢር ነቢዩ ቅዱስ
ዳዊት በመዝሙሩ “አሥር አውታር ባለው በገና እዘምርልሃለሁ።” ያለውን ምሳሌ በማድረግ ነው። (መዝ ø¿£፥፱) እነዚህም ምልክቶች
ድፋት፣ ሂደት፣ ቅናት፣ ይዘት፣ቁርጥ (ቁርጽ)፣ ጭረት፣ ርክርክ፣ ደረት፣ አንብር፣ ድርስ ናቸው። በቅዱስ ያሬድ ዘመን ይሠራባቸው
የነበሩት የመጀመሪያዎቹ ስምንት የዜማ ምልክቶች የነበሩ ሲሆን ከርሱ በኋላ በነበሩ ሊቃውንት ደግሞ ሁለቱ ማለትም ድርስ እና አንብር
የተሰኙት ሁለት ምልክቶች ተጨምረዋል።
የቅዱስ ያሬድ ዜማ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት በማጠናከርና በመጠበቅ ረገድ የሚሰጠው ጥቅም ከፍተኛ ነው። ይኸውም በየትኛውም
አካባቢ የምትገኝ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድ ዓይነት የቅዳሴ ዜማ ያላት በመሆኗ ይታወቃል። በመሆኑም ይህን ቅዱስ ዜማ
መንከባከብ ይጠበቅብናል።
ርእሰ ደብር ብርሃኑ አካል