22 ተኛው ዓመታዊ ጉባኤ – የዕለተ አርብ
በኢ/ኦተ/ቤ/ክ በሰሜን አሜሪካ አኅጉረ ስብከት የሰንበት ትቤቶች አንድነት ጉባኤ
22 ተኛው ዓመታዊ ጉባኤ በርእሰ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አርብ ነሔሴ 27 ከምሽቱ 6:00 pm ተጀመረ።
የደብሩ (የካቴድራሉ) አስተዳዳሪ መልአከ አርያም አባ ኃይለ ሚካኤል
መልአከ ሰላም ቀሲስ መስፍን (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች አባቶች እና ከየክፍለ ከተማው የመጡ የሰ/ት/ቤት አባላት በተገኙበት በሠርክ ጸሎት መርሃ ግብሩ ተጀምሯል።
በማስከተልም “ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ”
“በአባቶች ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ” መዝ 44፥16
የሚለው ምስባክ ተሰብኮ በማስከተልም በርእሰ ደብር ብርሃኑ አካል
“እነሆ የጠራኸኝ” 1ኛ መ ሳሙ 3፥5
በሚል ኃይለ ቃል ትምህርት አስተላልፈዋል።
የሰ/ት/ቤቱ ሊቀ መንበርም የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
ላለፉት 3 ዓመታት በመላው ዓለም በተከሰተው ወረርሽኝ ምክንያት ጉባኤውን በአካል ማድረግ ባይቻልም ዘመኑ የፈጠረውን የመገናኛ ዘዴ በመጠቀም ዓመታዊ ጉባኤው ተካሂዷል።
እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በ2014 ዓ/ም አንድነት ጉባኤው በተመሠረተበት ቤዛ ኩሉ ሰ/ት/ቤት አዘጋጅነት ለሚቀጥሉት 3 ቀናት ጉባኤው የሚቀጥል ሲሆን የዕለቱን ክንውኖች እየተካታተልን የምንዘግብ መሆናችንን እንገልፃለን።