የዕለተ ቅዳሜ – 22 ተኛው ዓመታዊ ጉባኤ
የ2ተና ቀን ጉባኤ ተካሄደ
ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣጤዎስ የሚኒሶታ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት እንዲሁም የኢሊባቡር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጉባኤውን በጸሎት ከፍተዋል።
መልአከ አርኣያም አባ ኃይለ ሚካኤል
መጋቤ አዕላፍ ቀሲስ ስንታየሁ
መልአከ ሰላም ቀሲስ ዶ/ር መስፍን ተገኝ
እንዲሁም አበው መነኮሳት ፣ ቀሳውስት እና ከ10 ከተሞች የመጡ 16 በላይ የሆኑ ሰ/ት/ቤቶች አባላት በዚህ ጉባኤ ላይ ተሳትፈዋል በዕለተ ቅዳሜ መርሃ ግብር ላይ የአንድነት ጉባኤው የዓመቱ የሥራ ዘርዝር ሪፓርት እና የሦስት ዓመት አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ዘገባ፣ መስማት የተሳናቸው አባላት የሥራ እንቅስቃሴ፣ መንፈሳዊ ተውኔት፣ በሥራ አመራር እና የአይምሮ ደህንነት የተመለከተ ጥናታዊ ጽሑፎች እና ሌሎች መርሃ ግብሮች ተካሂደዋል።
“በጊዜውም ያላ ጊዜውም ጽና” 2ተኛ ጢሞ 4፥2 በሚል ኃይለ ቃል ቀሲስ ስንታየሁ ሰፋ ያለ ትምህርት አስተምረዋል። በተጨማሪም “በርታ ሰውም ሁን” መ/ነገሥት ቀዳማዊ 2፥3 በሚል ርዕስ በመልአከ ሰላም ቀሲስ ዶ/ር መስፍን ተገኝ ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቷል።
በአገልግሎት በፈተና በሕይወት ጉዞ ለሚመጡ ፈተናዎች ሳንበገር በርትተን ማለፍ እንዳለበን አስተምረዋል።
በሕጻናት እና አዳጊዎች መንፈሳዊ ሕይወት ዙሪያ የተደረገ ጥናት እንዲሁም የአይምሮ ደህንነት በሚል ርዕስ ጥናታዊ እንዲሁም የባለሙያ ትንታኔ ቀርቧል።
ከዚህ በተጨማሪ ላለፉት 5 ዓመታት በሥራ አመራርነት ሲያገለግሉ ቆይተው የአገልግሎት ጊዜያቸውን በፈጸሙ ወንድሞች እና እኅቶች ምትክ ምርጫ ለማድረግ የአስመራጭ ኮሚቴም መርጦ ሥራው ተጀምሯል። እንደተለመደው በየመርሃ ግብሩ ከተለያየ እስቴት የመጡ ሰንበት ተማሪዎች በተለይም ከሲያትል፣ ከሚኒሶታ፣ ከዲሲ እና አካባቢው የመጡ ተማሪዎች አጥንትን የሚያረሰርስ ጥዑመ ዜማ አሰምተዋል። በርካታ መርሃ ግብራት ከተካሄደ በኋላ ከምሽቱ 8:30 PM የዕለቱ መርሃ ግብር በጸሎት ተፈጽሟል።