ዘመነ ጽጌ

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ከልጅዋ እና ከወዳጅዋ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር መሰደድ፡-

በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል አብሳሪነት አምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ ነስቶ ወደዚህ ዓለም በመምጣት አምላካዊ ትእዛዝን ተላልፎ ካልተፈቀደለት ገበታ የተመገበውን እና በዚህም ምክንያት ከገነት የተሰደደውን አዳምን ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ ከተወለደበት ከሕፃንነቱ ጀምሮ ታላቅ የሆነ መከራ እና እንግልት ደርሶበታል፤ ሕማምን እና ስደትን ተቀብሏል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም የበኲር ልጅዋን ጌታችንን በወለደች በአርባኛው ቀኗ እንደ ኦሪቱ ሕግ መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ኢየሩሳሌም በሔደችበት ጊዜ አስቀድሞ ትንቢት የተነገረለትና በጌታም የተቀባውን ሳያይ ሞትን እንዳያይ በመንፈስ ቅዱስ ተረድቶ የነበረው አረጋዊው ስምዖን ጌታን ታቅፎ “እነሆ፥ የብዙዎች ልብ አሳብ ይገለጥ ዘንድ፥ ይህ በእስራኤል ላሉት ለብዙዎቹ ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው ለሚቃወሙትም ምልክት ተሾሞአል፥ በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል።” To read more click here