እንኳን ለዐቢይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ

ስለ ዐቢይ ጾም መጀመሪያ ሳምንት (ዘወረደ) ከማንሣታችን አስቀድመን ጥቂት ስለ ጾም እና መንፈሳዊ ሥርዓቱ እናወሳለን።

  • Tseme Diguaጾም ማለት ለዘለዓለም ሁሉንም ሕዋሳት ከኃጢአት መከልከል፣ ለተወሰነ ጊዜ ደግሞ እህል ከመብላት እና ውሃ ከመጠጣት መታቀብ ወይም ለተወሰኑ ወራት ከጥሉላት፣ ከሥጋ፣ ከወተት በአጠቃላይ ከእንስሳት ተዋጽኦ መከልከል ነው።
  • ጾም የሥጋ ምኞትን የምታጠፋ፣ የነፍስን ቁስል የምታደርቅ፣ ለጎልማሶችም ጸጥታን እና እርጋታን የምታስተምር፣ ከእንስሳዊ ግብር ጠባይ የምትከለክል እና ሰው መላእክትን መስሎ የሚኖርባት ደገኛ ሥርዓት ነች።
  • ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በዓመቱ ውስጥ ምእመናን መንፈሳዊ በረከትን እንዲያገኙ የተለያዩ አጽዋማትን ሥርዓት አድርጋ ሠርታልናለች። ከነዚህ አጽዋማት አንዱ እና ዋነኛው ዐቢይ ጾም ነው።

ዐቢይ ጾም

ይህ የጾም ወራት《ዐቢይ》 መባሉ ከአጽዋማት ሁሉ የላቀ መሆኑን ለማሳየት ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጾም ሳይገባው ለእኛ አርዓያ እና ምሳሌ ለመሆን በገዳመ ቆሮንቶስ የጾመው እና ዲያቢሎስን ድል የነሣበት በመሆኑ ነው። በሌላም መልኩ《ሁዳዴ》በመባል ይታወቃል። 《ሁዳድ》በሚለው ጥንታዊ ሰፊ የእርሻ መሬት ስም ታላቅነቱን ለመግለጽ ነው።

በዚህ የጾም ወራት በቤተ ክርስቲያናችን ጾመ ድጓ (ጾመ ምዕራፍ) ይቆማል፣ ዳዊት ይነበባል፣ ሥርዓተ ማኅሌቱ በመቋሚያ (በዝማሜ) ብቻ ይከናወናል። ወቅቱ የሱባዔ በመሆኑ በከበሮ እና በጸናጽል ሥርዓተ አምልኮ አይከናወንም። ዘወትር ስብሐተ ነግህ ይደርሳል። በሕማማት ሳምንት ደግሞ ትምህርተ ኅቡአት፣ ኪዳን ይተረጎማል፣ ትምህርተ ወንጌል ይሰጣል፣ ይጾማል ይሰገዳል፤ በሁለንተና ጌታ ይመለካል።

በጾሙም እንደ መድኃኒታችን ጠላትን ድል እንነሣበታለን። የጾሙ አቆጣጠርም በ《ኢየዐርግ》እና《ኢይወርድ》 የሚገደብ ሲሆን ሲወርድ ከየካቲት ፪ ቀን ፣ ሲወጣም ከመጋቢት ፮ ቀን  ጀምሮ እስከ በዓለ ትንሣኤ ዋዜማ ያለው ፶፭ ቀን ዐቢይ ጾም በመባል ይታወቃል።

በዐቢይ ጾም ውስጥ ፰ ሰንበታት ሲኖሩ ቅደም ተከተላቸውም እንደሚከተለው ነው፥

ዘወረደ                     ደብረ ዘይት

ቅድስት                    ገብርኄር

ምኩራብ                   ኒቆዲሞስ እና

መፃጉዕ                     ሆሳዕና ናቸው።

ዘወረደ

ዘወረደ ማለት《 የወረደ 》ማለት ሲሆን በዚህ ሳምንት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት፣ የሰው ፍቅር አገብሮት ከሰማያት መውረዱን፣ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የእኛን ሥጋ መዋሐዱን፣ ለአዳም በገባለት ቃል ኪዳን መሠረት የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ ከድንግሊቱ ተወልዶ በሥጋ መገለጡን (ዘፍ ፫፥፲፭ ፤ ፩ኛ ዮሐ ፫፥፰) የምናወሳበት ሳምንት ሲሆን በአጠቃላይ ዘወረደ ዕርቀ አዳም፣ ተስፋ አበው፣ ትንቢተ ነብያት ፣ ሱባዔ ካህናት የተፈጸመበት ፣ ኪዳነ አዳም መሲህ ክርስቶስ መወለዱን (በሥጋ መገለጡን) የሚነገርበት የፍቅር አዋጅ ነው። ስያሜውም የተወሰደው በዕለቱ ከሚዘመርው የቅዱስ ያሬድ መዝሙር ነው። … ተጨማሪ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

  ሥልጠናውን ለመውሰድ እዚህ ይመዝገቡ

To join the training click the link …..
https://www.freeconferencecall.com/…/pipi…/start_application

 

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ
“ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።”
                                          (ማር ፲፮፥፲፮)

 

 

 

 

 

 

 

“አንድ ጌታ አንድ ይማኖት አንዲት ጥምቀት” ኤፌ፬፥፭

ጥምቀት ቃሉ የግዕዝ ሲሆን አጥመቀ ከሚለው ግሥ የተገኘ ነው። ትርጉሙም በገቢር መንከር፣መድፈቅ መዝፈቅ በተገብሮ ሲሆን ደግሞ መነከር፣ መደፈቅ፣ መዘፈቅ፣ መላ አካልን በውሃ ውስጥ ገብቶ መውጣት ማለት ነው። የጥምቀት በዓል ዋዜማው “ከተራ” በመባል ይታወቃል። ከተራ ማለት መገደብ ማለት ነው። ታቦታተ ሕጉ ከመንበረ ክብራቸው ተነሥተው በወንዝ ዳር ወይም በሰው ሠራሽ የውሃ ግድብ ዳር በዳስ/በድንኳን ውስጥ ያድራሉ፡፡ የጥምቀት በዓል መነሻው የጌታችን የመድኃኔታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መጠመቅ ነው፡፡ ጌታችን የተጠመቀው ለአዳምና ሔዋን ድኅነት ሲል ነው፡፡

አዳምና ሔዋንን ሰይጣን በእባብ አማካይነት አትብሉ የተባሉትን ዕፀ በለስ በስሕተት እንዲበሉ አድርጎ፣ ዕፀ በለስን በመብላታቸው ምክንያት በሞተ ሥጋ ላይ ሞተ ነፍስ በርደተ መቃብር ላይ ርደተ ገሃነመ እሳት ተፈርዶባቸው ሳለ ዲያብሎስ የአባታችን አዳምና የእናታችን ሔዋንን የእዳ ደብዳቤ   አዳምና ሔዋን የዲያብሎስ ተገዢና አገልጋይ ብሎ ጽፎ በዮርዳኖስ ባሕርና በሲኦል ሸሽጎት ነበር። ለጥፋታቸውም ሥረየትን በጠየቁ ጊዜ እግዚአብሔር ተስፋ ሰጥቷቸዋል፡፡ ተስፋቸውም 5500 ዘመን ሲፈፀም ከልጅ ልጀህ ተወልጄ አድንሃለሁ የሚል ነበር። ይህን ተስፋ ለመፈፀም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከድንግል ማርያም ተወልዶ ፴ ዘመን ሲሞላው በዮርዳኖስ ተጠመቀ። የተነገረው ትንቢትና የተቆጠረው ሱባኤ ሲፈጸም በዮርዳኖስ ወንዝ በመጠመቅ የዕዳ ደብዳቤውን እንደ አምላክነቱ አቅልጦ እንደሰውነቱ ረግጦ አጥፍቶልናል፡፡ በሲኦል ያስቀመጠውንም በዕለተ አርብ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ አጥፍቶታል። ..… ተጨማሪ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን።

“ድንግልፈጣሪዋንወለደችው፣ እሱምእናቱንፈጠረ፣

እርሱም የፈጠረውን ሥጋ ተዋሐደ”

ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ቄርሎስ 

እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ

የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ቤ/ክ ሰ/ት/ቤ/ት ትምህርት ክፍል – ቨርጂኒያ/ታኅሣስ 2011 ዓ.ም/

“ዛሬ በዳዊት ከተማ፣መድኃኒት፣እርሱም ክርስቶስ፣ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል” ሉቃ. 2፥14

ይህ ቃል የእግዚአብሔር መልአክ፣ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት ምሽት የተናገረው ቃል ነው። ይህ ቃል ከአዳም ጀምሮ የተነሡ ታላላቅ አበው ነቢያት ሊሰሙት ወደው ነገር ግን ያልሰሙት የምሥራች ቃል ነው። ነቢያቱ ሁሉ እግዚአብሔር አስቀድሞ ለአዳም “ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ” ብሎ የገባለትን የድኅነት ቃል ተስፋ በማድረግ ይህቺኑ ቀን ለማየት ሲመኙ በጾም በጸሎት ሲማጸኑ ኖረዋል። እናም ጊዜው ሲደርስ ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከነፍሷ ነፍስ ከሥጋዋ ሥጋ ነሥቶ አምላክ ሥጋ (ሰው) ሆኗል። ከላይ የተጠቀሰውም የመልአኩ ምስክርነት ይህንኑ የሚያስረዳ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ይህንኑ ሲያብራራ “ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ” በማለት ተናግሮአል (ገላ. 4፥4)። እዚህጋ እንደምናስተውለው መልአኩ “እርሱም ጌታ የሆነ” ብሎ ስለተወለደው ማንነት (አምላክነት) ሲገልጽልንና ሲያበስረን የዚህን የአምላክንመወለድ (ሰው መሆን) ምሥጢር ድንቅነትን እና የአምላክን ትሕትና ደግሞ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ከሕግ በታች የተወለደውን ልጁን” በማለት ገልጾታል። ለዚህ ትሕትናው ነው መላእክቱ በወቅቱ “ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ – ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ” በማለት ዝማሬ ያሰሙት (ሉቃ. 2፥14)። ይህንንም የሰማይ ሠራዊት ቅዱሳን መላእክት በጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት ምሽት የዘመሩትን የምስጋና ቃል ቅዱስ ያሬድ አንቀጸ ብርሃን በተሰኘው የጸሎት ድርሰቱ እንደሚከተለው አብራርቶታል። “ልጅሽንም በዚህ ዓለም በወለድሽው ጊዜ ዓይኖቻቸው ብዙዎች የሆኑ ኪሩቤል እና ክንፎቻቸው ስድስት የሆኑ ሱራፌል በበረት ውስጥ ጋረዱልሽ። የብርሃን ደመናዎችም ከበቡሽ የመላእክት አለቆች የመላእክት ሠራዊትና የሰማይ ጭፍሮች በመፍራትና በመንቀጥቀጥ በፊትሽ ቆሙ። በዚህም ዓለም ኪሩቤልና ሱራፌል በሰማያት ካለው ምስጋናቸው ወይም ከቀድሞ ምስጋናቸው ወገን ባልሆነ በሌላ (በአዲስ) ምስጋና አመሰገኑሽ። ፍጥረቱን ሁሉ ሰብስቦ የያዘና ፍጥረቱን ሁሉ የሚመግብ ጌታቸው በክንድሽ ተቀምጦ ጡትሽን እንደ ሕፃን ሲጠባ ባዩ ጊዜ በአርያም ፈለጉና በዚህ ዓለም እንደ ቀድሞው ከአባቱና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አገኙት። የጌታቸውን ትሕትና ባዩ ጊዜም ዓይኖቻቸውን ወደ ላይ ወደ አርያም ከፍ ከፍ አደረጉ ክንፋቸውንም ዘርግተው ‘ለሁሉ ጌታላንተ በሰማይ ምስጋና ይገባሃል’ እያሉ ጌታቸውን አመሰገኑ። ዳግመኛም በጎል ውስጥ አንቺን ከሕፃንሽ ጋር አይተው ‘በምድር ላይ ሰላም ፍቅር አንድነት ሆነ’ አሉ ካንቺ የነሣውን የኛን ሥጋ ለብሶ ባዩት ጊዜም ‘ሰውን ምንኛ ወደደው?’ ብለው ሰገዱለት።” አንቀጸ ብርሃን ቁ. 8።

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን ዓለም ከኃጢአት ሞት (ከጥንተ አብሶ) ሊያድን ወዶና ፈቅዶ ከሰማያት ወርዶ ከቅድስት ድንግል የተወለደው ደካማና ሟች የነበረውን የሰውን ልጅ ሊያበረታው፣ ሕያው ሊያደርገውና የዘላለም ሕይወት ሊያጎናጽፈው ነው። ይህም በመግቢያችን እንደተናገርነው የብዙዎች አበው ነቢያት ተስፋ፣ እንዲሁም ለእኛ በስሙ ለተጠራን ክርስቲያኖች ደግሞ አስደሳች የምሥራች ነው። ምክንያቱም እርሱ ጌታችን በመወለዱ እንደ ቅዱስ ቄርሎስ አገላለጽ “እንቲአሁ ለሥጋ ኮነ ለቃል፣ ወእንቲአሁ ለቃል ኮነ ለሥጋ – ሥጋ (ሰው) ያለው ነገር ሁሉ ለመለኮት ሆነ፣ እንዲሁም መለኮት ያለው ሁሉ ለሥጋ (ለሰው)” ሆኗልና ነው። አዎ ይህ ምሥጢር (ተዋሕዶ) ድንቅ ነው፣ ክቡር ነው። ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬምም የዚህን ምሥጢር ታላቅነት በረቡዕ ውዳሴ ማርያም ጸሎቱ እንዲህ በማለት ነበር የገለጸው። “እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ልዩ ከሆነች ከድንግልሰው ሆኗልና። ኑ! ይህን ድንቅ እዩ። ስለ ተገለጠልን ምሥጢር ምስጋና አቅርቡ። ሰው የማይሆን ሰው ሆኗልና። ቃል ተዋሕዷልና። ጥንት የሌለው ሥጋ ጥንታዊ ቀዳማዊ ሆነ። ዘመን የማይቆጠርለት መለኮት ዘመን ተቆጠረለት። የማይታወቅ ተገለጠ የማይታይ ታየ፣ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ በእርግጥ ሰው ሆነ። ትላንት የነበረው ዛሬም ያለው መቼም የሚኖረው ኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግድለትና እናመስግነው ዘንድ አንድ ባሕርይ ነው።” ውዳሴ ማርያም ዘረቡዕ ቁ. 7 ..… ተጨማሪ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ለጥምቀት በዓል የመዝሙር ጥናት በክፍለ ግዛቶች 

እንዘእግዚአብሔርውእቱሰብአኮነ፤ ወተወልደከመያድኅነነ፤

ወተጠምቀ ከመያድኅነነ

ሰላማዊ ብእሲሁ እደዊሁ ቅዱሳት ሰላማዊ ብእሲሁ
እለ አጥመቃሁ ለመድኃኔዓለም

 

ወደ አብነት ትምህርት ገጽ ለመሄድ እዚህ ያጫኑ