አንቀጽ 2፡- አከላለል :-

  • በሰሜን አሜሪካ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባዔ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 5 መሠረት ይህ የአንድነት ጉባዔ ተጠሪነቱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለሰሜን አሜሪካ ሀገረ ስብከት ይሆናል፡፡ የየክፍለ ግዛቶች ተጠሪነት ደግሞ በሀገረ ስብከቱ ሥር ላለው ለሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባዔ ሥራ አስፈጻሚ ይሆናል፡፡
  • የየቅርንጫፎች አከላለል በሰሜን አሜሪካ በሁሉም አካባቢ ያሉትን አብያተ ክርስቲያናት በ9 ቅርንጫፍ የከፈለ ነው፡፡ ወደፊት ግን የአንድነት ጉባኤው መዋቅር በተሞክሮ እየታየ ሲመጣና ሲጠናከር የአከላለሉ መሰረታዊ የሆኑ ነጥቦች ሊካተቱበትና እንደገና ሊታይ ይችላል፡፡

የክፍለ ግዛት ዝርዝርና በውስጣቸው የተካተቱት የሰሜን አሜሪካ ግዛቶች/ስቴቶች/ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

Slide11

የክፍለ ግዛቶች መዋቅርና የሥራ መመሪያ