ምን ሰጡህ ይሁዳ

መዝሙር ዘሆሳእና

ምን ሰጡህ ይሁዳ

ሙትን ልታስነሣ ድውይን ልትፈውሥ
ሥልጣን ሰጥቶህ ነበር ኢየሱስ ክርስቶስ
ልታስር ልትፈታ በነፍስም በስጋ /፪/
ሥልጣን ሰጥቶህ ነበር አልፋና ኦሜጋ/፪/
ምን ሰጡህ ይሁዳ አይሁድ ዘመዶችህ
ለእነርሱ አሳልፈህ ጌታህን የሰጠህ
ከሁሉ የሚበልጥ ሥልጣን ሰጥቶህ ሳለ/፪/
ብርን ለመቀበል ልብህ ተታለለ /፪/
ሰማይና ምድርን በቃል የፈጠረ
እንዴት በመቃብር ሦስት ቀን አደረ
አንተ የሰጠኸው አሳልፈህ ለሞት/፪/
ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ በሰንበት/፪/

ሆሳዕና(፪) በአርያም
ሆሳዕና በአርያምቅድስት ሀገር ሆይ ኢየሩሳሌም
ምስጋናሽ ብዙ ነው በመላው ዓለም
አዝ———

በአህያ ላይ ሆኖ ወዳንቺ የገባው
ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት ነው

አዝ———

ኃይልና ሥልጣን በአንድ ላይ ስላለው
ጠላቶች አፈሩ ሕዝብሽም ደስ አለው

አዝ———

ሰውማ ቢዘምር ምን ያስገርመናል
ሆሣዕና ሰው ቀርቶ ድንጋይ ያናግራል

አዝ——

 

መዝሙር ዘልደት

መዝሙር ዘብሥራት

 

 

 

 

 

 

 

 

 

መረጌታ ብርሃኑ ውድነህ

ዲ/ን እንግዳወርቅ በቀለ