ADDRESS

2216 Goldsmith Lane
Louisville, KY 40218

PHONE

502-749-8200

ዋና ገጽ/ HOME

 

የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተክርስቲያን አመሰራረት፣

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በእምነት የወለደቻቸው ልጆቿን ለመጠበቅና ለማፅናናት እንዲሁም የተልእኮዋ አንድ አካል የሆነውን እስክ አጽናፍ ዓለም ተጉዞ ያላመኑትን የማሰመን ያልተጠመቁትን የማጥመቅ ሥራ ለማከናዋን ከሀገር ውጭ አብያተ ክርስቲያናትን በመትከልና ካህናትን በመመደብ ሥትሰራ ቆይታለች። ከቤተክርስቲያኗ መመስረት ጋር አብሮ የተጀመረው የዚህ ሥራ ፍሬዎች የሆኑ የበርካታ አድባራትና ገዳማት ይዞታ በውጪው ዓለም ያሏት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በኢየሩሳሌም የሚገኙ አድባራትና ገዳማት ( የዴርሱልጣን ገዳም ) እንዲሁም በዚሁ በአሜሪካ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ትጠቃሾች ናቸው።
አብያተ ክርስቲያናትን የመትከልና ካህናትን መድቦ የቤተክርሲያኒቱን ተልእኮ የማስፋፋት ሥራ አድጎ ዛሬ በመላው  ዓለም በብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመሩ አህጉረ ሥብከታት፡በርካታ አድባራትና ገዳማት ባለቤት ለመሆን በቅታለች። የዚሁ ጥረት አካል የሆነው የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኢል ቤተ ክርሲቲያን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሃገረ ስብከት በልዊቪል ኬንታኪ ምስራቃዊ ክፍል የሚገኝ የቅድስት ቤተክርስቲያናችን ኩራት የሆነ ቅርስ ነው፡፡

ከሀገራቸው ተሰደው ከቤተክርስቲያን ተለይተው በመኖራቸው ምክንያት በየራሳቸው መንፈሳዊ ሕይወት ላይ የተከሰተውን መቀዛቀዝ፤ በቤተክርስቲያን እጦት ምክንያት በእምነት ወደ ማይመስሉን አብያተ ክርስቲያናት ያቀኑት የወገኖቻቸው እግሮች ፍፃሜ፤ ይልቁንም የራሱ ሃይማኖት፣ ዶግማ ፣ቀኖናና ትውፌት ፤የራሱ የሆነ ኢትዮጵያዊ ማንነት ያለው አዲሱ ትውልድ ከማህፅን ዮርዳኖስ እና ከአብራክ መንፈስቅዱስ በክርስትና የሚወለድበትና በራሱ ሃይማኖትና ኢትዮጵያዊ ማንነት የሚያድግበት እድል በማጣቱ የእንግዳ አስተምህሮ፣ የምዕራብያውያን የእምነትና የባህል ሰለባ ሲሆን የተመለከቱ ጥቂት የቤተክርስቲያን ልጆች ሻይ ቡና እየጠጡ የጀመሩት የ ” ምን እናድርግ “ውይይት አድጎ በአቅራቢያው ከሚገኘው ከኢንዲያናፖልስ ( Indianapolis ) ደብረሰላም ቅዱስ ሚካኢል ቤተክርስቲያን ካህናት ጋር፤ ቀጥሎም በዚህ የጥቂቶች ስብስብ ይልቁንም በእየአንዳንዱ የቤተክርስቲያን ልጅ ልብ ውስጥ ” በእግዚአብሔር ሁሉም ይቻላል ” የሚል ጠንካራ እምነት ተክለው፤ ጥቂቶቹን አሰልፈው የዚህ ሠፊ ይዞታ ፣የዚህ ታላቅ የሃገርና የወገን ኩራት ይሆነ ቅርስ ባለቤት መሆን ይቻል ዘንድ የመንፈሳዊ ተጋድሎው ፊታውራሪ ከሆኑት ከወቅቱ የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከብፁእ አቡነ አብርሃም ጋር መገናኘት ቻሉ፡፡

ብፅዕ አቡነ አብርሃም ለልጆቻቸው ጥያቄ ተገቢ ምላሽ በመስጠት ካህን መድበው የቅዱስ ገብርኤልን ታቦት አስይዘው ላኩ። ህልም ይመስል የነበረው እውነትም እውን መሆን ጀመረ። በካቶሊክ ቤተክርሲያን ብጎ ፈቃድ በተገኘ ጊዚያዊ ስፍራ እሁድ ከማለዳ እስከ ረፋድ የሚሰጥ ሳምንታዊ የቅዳሴ አገልግሎት ተጀመረ። በዚህ ሁኔታ የቀጠለው አገልግሎት አድጎ ታቦተ ህጉ የራሱ መንበር ኖሮት እንዲያርፍ፤ አገልግሎቱ እንዲሰፋ እና አማኞቹም የራሳቸው መሰባሰቢያ እንዲያገኙ ለማድረግ ጥረቱ ቀጠለ። ይህ ጥረት ሊቀጳጳሱን በረጅምና አሰልች ጉዞ፣ ባልተሟላ የጤንነት ሁኔታ በወር ሁለትና ሶስት ጊዜ ከዲሲ ኬንታኪ ያመላለሰ፤ በቦታው የነበሩ ካህናትን ሌት ተቀን ያሰራ፤ ምእመናን ግላዊና ቤተሰባዊ ሕይወታቸውን ረስተው ለዚህ ጥረት መሳካት ብቻ እንዲሰሩ ያደርገ ነበር። ምንም እንኳን ሰው የፈለገውን ያህል ቢመኝ፣ ቢሰራና ቢደክምም የእግዚአብሔር ቤት ካለ እግዚአብሔር ፈቃድ አይሰራምና ፤ከላይ እስከ ታች ባሉ ካህናትና ምእመናን አድሮ ይሰራ የነበረው እግዚአብሔር በገድልና ተአምራት ከምናነበው እና ከሚያስደምመን ለቀደምት አባቶቻችን የተደረገ ታምራት በማይተናነስ ሁኔታ በውጭም በሻጭዎች እና በሌሎች ጉዳዪ በሚመለከታቸው ወገኖች ላይ አድሮ በግልጽ ሲሰራ እየታየ የዚህ ታላቅ ይዞታ ባለቤት በመሆን ተጠናቀቀ። ጥቂት አባላት፣ ያልዳበረ የግዥ ታሪክ( credit history ) ምንም ሊባል የሚችል የባንክ ተቀማጭ ይዞ ጠንካራውን የሃገሪቱን የሽያጭ ህግጋት አሸንፎ የሻጮችን የማይታሰብ ድጋፍ በማግኝት የዚህ ይዞታ ባለቤት መሆን በምንም መለኪያ ተአምር እንጅ ምን ሊሆን ይችላል?

 

101_3057 - CopyDSC00221 - Copy

 

 

 

91 comments on “ዋና ገጽ/ HOME

 1. Pingback: daily boat rentals
 2. Pingback: gogoanime.digital
 3. Pingback: movies123
 4. Pingback: live draw hk
 5. Pingback: Dekbedovertrekken
 6. Pingback: Cbd For Men
 7. Pingback: pr jobs
 8. Pingback: Betrug
 9. Pingback: Energy Plans
 10. Pingback: 먹튀검증
 11. Pingback: Attitude Seeds
 12. Pingback: 메이저바카라
 13. Pingback: Nagad
 14. Pingback: influencemi
 15. Pingback: warnetqq
 16. Pingback: gclub
 17. Pingback: MJ Notary Denver
 18. Pingback: similar
 19. Pingback: xs quang ngai
 20. Pingback: w88hello
 21. Pingback: Qənnadı şokolad
 22. Pingback: additional reading
 23. Pingback: shapeforu
 24. Pingback: Auto Repair Shop
 25. Pingback: How to lose weight
 26. Pingback: Testing 55
 27. Pingback: Testing56
 28. Pingback: Testing57
 29. Pingback: Spring cnc machine
 30. Pingback: find a landscaper
 31. Pingback: China micro switch
 32. Pingback: limit switch price
 33. Pingback: China Micro Switch
 34. Pingback: olansi global
 35. Pingback: Nguyen bean Lang
 36. Pingback: qqslot
 37. Pingback: lk21 duniafilm21
 38. Pingback: depoxito slot

Leave a Reply