በቤተክርስቲያናችን የሚሰጡ አገልግሎቶች፤
የሰው ልጆች የተፈጠርንበት ዋነኛ ዓላማ ምስጋና የባህሪው ለሆነው ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ማቅረብ ነው። ሰንዱ እናታችን ቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆችዋ በማህበር አምላካቸውን የሚያመሰግኑባት፣ ሀብተ ወልድና ስመ ክርስትናን የሚያገኙባት፣ ይህn ታላቅ ፀጋ ያገኙ አማንያን ልጆችዋ በመንፈሳዊ ዕውቀት የሚያድጉባት፣ ምግባር ትሩፋትን መስራት የሚማሩባት በአጠቃላይ የፀጋ ግምጃ ቤቷ ሀብት የሆኑ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን የሚያገኙባት በምድር ያለች የእግዚአብሔር ቤተ መንግስት ናት። ምንም እንኳ በዚህ መሰረታዊ እውነታ ላይ ተመስርተን ሊሰጡ የሚገባቸውን ሁሉንም አገልግሎቶች ባለብን የሰው ኃይል ቁሳዊ አቅም ውሱንነት ምክንያት መስጠት ባንችልም ያለንን ጥቂት የሰው ኃይል፣ ውስን ቁሳዊ አቅምና ምቹ ሁኔታ ተጠቅመን የሚከተሉትን ዋና ዋና አገልግሎቶች እንሰጣለን፦
- የቅዳሴ አገልግሎት በዓበይት በአላትና በዕለተ ሰንበት በዕለተ ሰንበት /እሁድ/፣ ፆም በማይፆምባቸውና በጠዋት በሚቀደስባቸው ዕለታት ከሌሊቱ 4:00 AM እስከ ቀኑ 11:00 AM ፣ በአጽዋማትና ከሰዓት በኋላ በሚቀደስባቸው ዕለታት /ከሰኞ – አርብ፣/ ከ 11:00 AM -3:00 PM፤
- ስብሓተ ነግህ /የጠዋት ጸሎት/ በየዕለቱ 5:00AM እስከ 8:00 AM፤
- የሰርክ ጸሎትና / የምሽት ፀሎት/ ትምህርተ ወንጌል ከ6:00PM- 7:30 PM፤
- ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች፣ ከካናዳና ከአውሮፓ ለሚመጡ ምእመናን የጸበል ማጥመቅ /ፈውስ አገልግሎት/ ከሰኞ- ቅዳሜ ከ6:00 AM- 8:00 AM እሁድ ከ5፡00 6:00 AM፤
- ምክረ ካህን በዕየለቱ በመደበኛ አገልግሎት ባልተሸፈኑ ጊዜያት፤
- በተጨማሪም ከርቀት ለሚመጡ እንግዶች የመኝታ አገልግሎት እንሰጣለን። ያለን ቦታ ሲሞላ (ወይም ከልጆች ጋር ለሚመጡ) በአቅራቢያው ባለው ሆቴል ያርፋሉ::
- በእሁኑ ወቅት የማረፊያ ቦታው እድሳት ላይ ስለሆነ ምንም የማረፊያ ቦታ የለንም። እባክዎን ከመምጣትዎ በፊት ሆቴል ይያዙ።
- PLEASE NOTE: CURRENTLY ALL OUR GUEST ROOMS ARE UNDERGOING MAINTENANCE; THEREFORE, WE HAVE NO ROOMS FOR ANY GUESTS TO STAY IN UNTIL FURTHER NOTICE. PLEASE MAKE SURE YOU HAVE RESERVED A HOTEL NEAR BY BEFORE YOUR ARRIVAL TO OUR CHURCH. SEE LIST BELOW FOR NEAR BY HOTELS.
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
Servcie Hours
Daily Prayer Service:
Monday—Saturday
5:00 AM to 7:00 AM
And
6:00 PM to 7:30 PM
Sunday
4:30 AM to 11:00 AM
And
6:00 PM to 7:30 PM
Holy Water Service
Mon to Sat: Starting 6:00 AM
Sunday: Starting 5:00 AM
48 comments on “አገልግሎት/Service”