ADDRESS

2216 Goldsmith Lane
Louisville, KY 40218

PHONE

502-749-8200

ጸበል በአሜሪካ/ Holy Water

የፀበል አገልግሎት፣

አጠቃላይ እይታ

ደዌ ስጋና ንፍስን የምታክም ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ደዌ ንፍስን በንስሃ፣ በመክረ ካህን፣ ቀኖና እና በስጋወደሙ እንደምታድን ሁሉ ደዌ ስጋንም በፀበል፣ እምነት፣ ዘይት ( መስጢረ ቀንዲል ) እያከመች ስትፈውስ ቆይታለች:: ዛሬም ወደፊትም ትፈውሳለች። ስንዱ እናታችን ቅድስት ቤተክርስቲያን በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በልዩ ልዩ ምክንያት የተበተኑ ልጆቿ ከዚህ ፀጋ ተካፋይነት እንዳይለዩ ክርስትናን አግኝተው ከሥላሴ ተወልደው የተሰደዱትን በእምነታቸው ለማፅናት፣ በፈተናቸው ለማፅናናት እና ለመጠበቅ በባእድ አገር የሚወለደው አዲስ ትውልድም ከቅድስት ቤተክርስቲያን የሚወለድበትን እድል ለመፍጠር ልጆቿን ተከትላ በመላው ዓለም አገልግሎት በመስጠት ላይ ትገኛለች።

መንጋውን የመጠበቅ ኃላፊነት በወደቀባቸው የቤተክርስትያን አባቶችና በማህበረ ምዕመናን ድካም ቁጥሩ በርከት ያለ ኢትዮጵያዊ በሚገኝባቸው ከተሞች አብያተ  ክርስትያናት ገዝቶም ሆነ ሰርቶ ቤተክርስትያን የምትሰጣቸውን አገልግሎቶች ተጠቃሚ መሆን የተቻለ ቢሆንም እንኳ በተለይ ያመመው የጨነቀው ሰው በቅርቡ ካሉ አብያተ ክርስትያናት የሚፈልገውን እያጣ ህሊናው በምኞት ወይም በሃሳብ አክናፍ ተጭኖ ወደ ሃገር ቤት የሚኮበልለው  ክርስቲያን ቁጥሩ የትየለሌ ነው::

ፀጥ ረጭ ያለ ግቢ፣ እድሜ ጠገብ አፀዶች፣ በርጋታ ገብተው፣ በተመስጦ ፀልየው፣ ፀበሉን ቀምሰው፣ አቧራውን ልሰው ፣ተስፋ ሰንቀው የሚመለሱ ምእመናን፤ የአዕዋፍ ዝማሬ፣ ሄድሮስ ያስፈጃቸው አዕላፍ ሕፃናት የሚመሰሉባቸውና በቤተክርስትያኑ ጣሪያ ላይ የተሰቀሉ ትንንሸ ቃጭሎች [ሻኩራዎች] በነፋሰ እየተገፉ የሚፈጥሩት ድምፅ፤ ሰላማዊ ግቢ ውስጥ መሆንን የምንናፍቅበት ጊዜ ብዙ ነው:: ህሊናችንን  የሚፈታተን ኮሽታ በሌለበት ዛፍ ተደግፈን ወይም ግድግዳውን ተጠግተን አልቅሰን ፣ ፀልየን ፣ተስለን ወይም ከፀበሉ ተጠምቀን የተሸከምነውን አራግፈን  በነፃነት ለመወጣት እንናፍቃለን::  ከዚህ ተመስጦ ወደ ህሊናችን ተመልሰን እናእሳ ለምን ? ስንል ወጭው የጊዜና የሁኔታዎቹ ፈተና ጠርንቆ ይይዘንና የሃሳብ  ጽንሳችን  እየጨነገፈ  የምንፈልገውን  አጠተን  ከማንፈልገው  ጋር  ተጣጥመን ትላንትን ያሳለፍን ጥቂቶች አይደለንም ::

እንደሚታወቀው በምንኖርበት ሃገር አብያተ ክርስቲያናቱ  የሚታነጹት በጠባብ ይዞታ ላይ ለመንገድ እጅግ ተጠግተው ስለሆነ እድሜ ጠገብ ዛፎችና በሳር የተሸፈነ መሬትም ማየት አዳጋች ነው፡፡ ጥቂት ቦታ እንኳ ቢገኝ  ለመኪና ማቆሚያነት (parking) ስለሚያገለግል አፀድ አልባ ግቢ ውስጥ ተገኝተን እኛ የምናውቀውንና  የለመድነውን የቤተክርስቲያን ድባብ ስለምናጣ  በተመስጦ ለመፀለይ ፀጥታችን የሚያውከው ባእድ እንቅስቃሴ ትኩረታችንን ይፈታተነዋል:: ከዚህም አልፎ አንዳንዶቹን ወሳኝ የቤተክርስትያን አገልግሎቶች ከምድሩ ጫፍ እስከ ጫፍ ብንጓዝ አናገኛቸውም:: የህመሙ ፈውስ ዘመናዊው መድሃኒት ሳይሆን ፀበል እንደሆነ የሚያውቅ፣ የህክምና ተቋማቱን በድፍረት ለመጎብኘት የጤና ዋስትና (insurance) የሌለው ፣የገንዘብ አቅሙ ድፍረት ያሳጣው ወገን ወይም የህክምና ተቋማቱን በር አንኮኩቶ ምክር እና መድሃኒታቸውን ተጠቅሞ ምፍቲሄ ያጣ ፡ወገን እድሜ ለፀበል ቢል፡ ፀበል ማግኘት ከህክምና ተቋማቱ የማይተናነስ ወጭ ሲጠይቀው ሰንብቷል :: ዛሬ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉንም እዚሁ ደብረ ኋይል ቅዱስ ገብርኤል  ማግኘት ይቻላል:: “ምን ም አላችሁ?”  ካሉን   ቆይታዎን ከኛ ጋር ያድርጉ፦

፩/ ፀጥ ረጭ ያለ ሰላም የሰፈነበት ግቢ

እዚህ አገር ከተለመደው የቤተ ክርስቲያን አሠራር በእጅጉ ይለያል   የደብረ ኋይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ያረፈው በ ፭ ሔክታር ይዞታ ላይ ነው። ይህ ሠፊ ይዞታ በለምለም ሣርና የአገር ቤቷን ቤተክርስቲያን በሚያስታውሰንና ያንኑ ድባብ በሚፈጥሩ እድሜ ጠገብ ዛፎች ተሸፍኗል። ይህን ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው አካባቢውን መኖሪያ ያደረጉ አዕዋፍ ከሚያሰሙት ዝማሬ ውጭ ግቢው በፀጥታ የተሞላነው። ቤተክርስቲያኑ ከዋና ዋና መንገዶች ራቅ ብሎ በመታነፁ ይህን ሠላምና ፀጥታ የሚያውክ አንድም ነገር የለም። በመሆኑም ቦታው  በግርግርና ሁካታ በተሞላ ዓለም ሠላም ላጣና ለታወከ አዕምሮ ሰላም፤ በዕርጋታና በተመስጦ  ለመጸለይ ወይም  ጠይቆ  ለመቀበል የሚያስችል የእግዚአብሔር ቤት ነው።

፪/ ምቹ ማረፊያ

ለእንግዳ ማረፊያ በቤተክርስቲያኑ አጥር ግቢ ውስጥ የተዘጋጁ በቂ ክፍሎች ስላሉ ሡባዔ ለመግባት፣ ፀሎት ለመያዝ ወይም ፀበል ለመፀበል ወደ ቤተ ክርስቲያኑ የሚመጡ ምዕመናን ስለ ማረፊያ መጨነቅ አይኖርባቸውም።  በአንድ ጊዜ በርካቶች ሊጠቀሙበት የሚችሉበት ኩሽና (kitchen)፣ ይዘው የመጡትን ሥንቅም ሆነ ያበሰሉትን  ምግብ የሚያስቀምጡባችው ማቀዝቀዣዎች፣ ዝግጁ የመታጠቢያ  ቤቶች ሥላሉን  ፈልገው የሚያጡት ነገር የለም :: በአጠቃላይ የሡባኤ፣ የፀሎት  ወይም የፀበል ቆይታዎን አቋርጠው በሁኔታዎች  አስገዳጂነት ግቢውን ለቀው ለአፍታም እንኳ አይወጡም :: ቤቱ ሁሉም የተሟላለት ነው::

 •  በእሁኑ ወቅት የማረፊያ ቦታው እድሳት ላይ ስለሆነ ምንም የማረፊያ ቦታ የለንም። እባክዎን ከመምጣትዎ በፊት ሆቴል ይያዙ።
 • PLEASE NOTE: CURRENTLY ALL OUR GUEST ROOMS ARE UNDERGOING MAINTENANCE; THEREFORE, WE HAVE NO ROOMS FOR ANY GUESTS TO STAY IN UNTIL FURTHER NOTICE. PLEASE MAKE SURE YOU HAVE RESERVED A HOTEL NEAR BY BEFORE YOUR ARRIVAL TO OUR CHURCH. SEE LIST BELOW FOR NEAR BY HOTELS. 

፫/ እንግዳ ተቀባይ ምዕመናን

ደብረ ኋይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን መጥተው የተመለሱ ሁሉ ሶስት ቃላትን በያዘ አንድ አረፍተ ነገር ይስማማሉ “እንግዳ አቀባበልን ታውቁበታላችሁ” ይላሉ። ሰለተደረገላቸው መስተንግዶም “ እግዚአብሔር ይህንን  ፍቅርና መግባባት አያሳጣችሁ፣ እግዚአብሔር ደብራችሁን ይጠብቅላችሁ” በማለት ይመርቃሉ። ወደ ቤተ ክርስቲያኑ የመጡ ሁሉ በቆይታችው  የእንግድነት ስሜት እንዳልተሰማቸው  በተደጋጋሚ ምስክርነታቸውን ሰጥተውናል። ከእንግዶች በተደጋጋሚ የሚሰጡ ገንቢ አስተያየቶች እኛን የቤተ ክርስቲያኑ አገልጋይ ምዕመናንንም በእምነታችን የበለጠ  እንድንተጋና ለነፍሳችን እንድንሰራ አድርጎናል። በርካታዎቹ ምእመናን ሁለት ጊዜ አልቅሰው ይሄዳሉ። ሲመጡ የተሸከሙት ደዌ፣ የሰሙት ተስፋ፣ በዚህ ግዙፍ ግቢ ውስጥ የሚኖራቸውን የብቸኝነት ቆይታ እያሰቡ የተናገራቸው ሁኖ የተሸከሙትን ጥለው በተሞላ ጤንነት ይመለሱ ዘንድ እየለመኑ በልቅሶ ይገባሉ። ሲወጡ በተደረገላቸው ድንቅ ነገር ረክተው፣ በቆይታቸው ተደስተው፣ የእግዚአብሔርን የማዳን እጅ አይተው፣ ሸክማቸውን ጥለው የደስታ ሲቃ የእርካታ እንባ ያነባሉ። መሄዳቸው የግድ ነውና ልባቸው ወደኋላ ቀርቶ እግራቸው ወደፊት ይራመዳል።

/ ለማገልገል የተዘጋጁ ካህንናት

ካህናቱ የአካባቢውን ምዕመናንም ሆነ የእንግዶችን ሀሣብ ለማዳመጥ፣ ንሥሃ ለመቀበል፣ ለመምከር፣ ለማፅናናት፤ ለጸበልና ሌሎችም አገልግሎቶች ሁሌም ዝግጁ ሲሆኑ የቤተክርስቲያኑም ዲያቆናት በአገልግሎት ሁሌም አብረዋቸው ናቸው። ሰው የከበደ ሸክሙን ለማራገፍ፤ የቆሸሸና ያደፈውን ለማፅዳት ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲመጣ ካህናት የእግዚአብሔር እንደራሴ በመሆን ይጸልያሉ፣ ያጽናናሉ፣ ይመክራሉ፤ ይገስጻሉም። ካህናቱ የታመመውን በፀበል መንፈሱ የታወከውን ችግሩን በማድመጥ፣ በመምከርና በማጽናናት ንስሃ በመቀበል ሸክሙን አቅልለው ደስታና ሰላምን አጎናጽፈው እንዲመለስ በማድረግ ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን አደራ በመወጣት ላይ ይገኛሉ።

፭/ የፀበል አገልግሎት

የደብረ ኋይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በሰሜን አሜሪካ  የመጀመሪያውና ብቸኛው  የፀበል አገልግሎት የሚሰጥበት ቤተክርስቲያን ነው። የፀበሉ  እዚህ መኖር በገንዘብና ጊዜእጦት ወይም በሁኔታዎች  አለመመቻቸት አገልግልቱን  እየናፈቁ  አጥተው ለኖሩ ምዕመናን ታላቅ መልስ ነው። ፀበሉ በወቅቱ የዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በነበሩት ብፁዕ አቡነ አብርሃም ተባርኮ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ጀምሮ ከአካባቢውና ከርቀት የሚመጡ ምዕመናን በዘመናዊ ህክምና ጭምር ሊረዱ ካልቻሉበት የተለያዩ በሽታዎች ተፈውሰዋል።  ባለፉት ጥቂት አመታት በደብሩ የሚኖሩትም ሆነ ከከተማ  ውጭ የመጡ ምዕመናን በሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት በእግዚአብሔር ቸርነት የተሸከሙትን የሃሳብ ሸክም አራግፈው ከህመማቸው ተፈውሰው ተመልሰዋል:: እርሥዎስ? በጭንቀት ወይም Stress ውስጥ እየኖሩ ከሆነ ለምን? ፀበል የሚናፍቁበት ህመም አግኝቶትስ ቢሆን እስከ መቼ ይናፍቃሉ? ዛሬ በእግዚአብሔር ቸርነት ጭንቀቶትን አራግፈው ሰላም ተጐናፅፈው ወይም ከህመም ተፈውሰው በተሟላ  ጤንነት ለመመለስ ዋስትና የሆነ ፀበል እዚህ አለ:: ቃላችን ከነባራዊ እውነት ጋር ፍፁም አንድ ነው መጥተው ይዩ! መጥተው ይፀበሉ! መጥተው ይፈወሱ!

 Tsebel bota

49 comments on “ጸበል በአሜሪካ/ Holy Water

 1. Pingback: residential proxy
 2. Pingback: cach vao 12bet
 3. Pingback: vn88 cuc manh
 4. Pingback: opinie
 5. Pingback: tempobet
 6. Pingback: child porn
 7. Pingback: gay porn
 8. Pingback: Scanner
 9. Pingback: 12betvn88
 10. Pingback: cach choi lo
 11. Pingback: best-123movies.com
 12. Pingback: solarmovie.gallery
 13. Pingback: vao 12bet
 14. Pingback: child porn
 15. Pingback: tai bingo
 16. Pingback: Dab rig
 17. Pingback: qq online
 18. Pingback: ca cuoc m88
 19. Pingback: Michael Lutz
 20. Pingback: rajaqq
 21. Pingback: warnetqq
 22. Pingback: huong dan vao m88
 23. Pingback: w88dn
 24. Pingback: dang nhap 188bet
 25. Pingback: melbourne removals
 26. Pingback: 188bet 512
 27. Pingback: m88bet.com
 28. Pingback: m88asia.com
 29. Pingback: raja dewaqq
 30. Pingback: Cam Girls

Leave a Reply